በበጎ ፈቃደኝነት ተነሳሺነት ፣ በፈረንሳይ ኗሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያኖችና በፈረንሳይ ተወላጅ ጓደኛሞች መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ በችግር ላይ ወድቀው ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችና ት/ቤቶች ፣ ያለባቸውን ችግር አብረዋቸው ለመካፈል ፣ የፈረንሳይ 1901 ዓ/ም ሕግ በሚፈቅደው መሠረት በአውሮፓውያን ቀን አቆጣጠር በ ሐምሌ 18 - 1996 ዓ/ም « Association Bourgeons » ፣ ሲነበብ ‘’ቡርዦ’’ ሲተረጎም ደግሞ ‘’ እንቡጥ’’ በሚለው ስም ማኅበሩ ተሰይሞ ተቋቋመ :: በዚህ ሕግ አንቀጽ 1901 ስር የሚተዳደሩ ማኅበሮች ምንም የመተዳደሪያ ገቢ የሌላቸው ወይም በንግድ ዓለም ተሰማርተው አትራፊ ያልሆኑ  ግብረሰናይ ማኅበሮች ናቸው ::
ስለዚህ እንቡጥ ወይም Bourgeons በዚህ ሕግ ስር የሚተዳደር በመሆኑ ፣ በመዋቅሩ ደረጃ ፣ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም (NGO / Non-Governmental Organization) ያልሆነ በመሆኑ ፣ ከሌላ የውጭ ድርጅት ምንም ዓይነት ገቢ የሌለው ሲሆን ፣ የገንዘብ መዋጮ ፣ የጉልበት ፣ የዕውቀት ና የነጻ አገልግሎት ፣ ከበጎ አድራጊ አባሎቹ በሚሰጠው ልገሳ የሚተዳደር ፣ በበጎ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የወንድማማቾች ማኅበር  ነው ::

መላው የእንቡጥ ማኅበር አባላት በቅድምያ ሰላምታችን ይድረሳችሁ
እንደሚታወቀው የእንቡጥ ማኅበራችን ከምስረታው ግዜ ጀምሮ በአባላቱ ፣ በኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ተራ በተራ ርዳታ ፣ እንዲሁም የምንኖርበት መዘጋጃ ቤት ይኽን ሁሉ ዓመታት ነጻ የመደገሻ አዳራሽ ፈቃድ በመስጠት ወዘተ እየተረዳ አመታትን እያሳለፈ ይገኛል ።  በዚህ አኳያ በማኅበሩ ጥላ ስር በዕውቀት እየበለጸጉ በተለያየ ሙያ ተሰማርተው ራሳቸውን የቻሉ ተማሪዎች ብዙሓን ናቸው ። ታድያ በነዚህ ትጉህ ተማሪዎቻችን እየኮራን ፣ ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለዚህ በጎ አድራጎት ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ጥልቅ የሆነ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን ። ትምህርት ለሌላው የሚተላለፍ የማይሞት ሃብት ነውና !!
በዚኽ አርስት ላይ ካላችሁ ግዜ ትንሽ ተበድራችሁ ‘’ የእንቡጥ ማኅበር ለማንና ለምን ተመሠረተ ‘’ የሚለውን ታሪካዊ ሂደት ብታነቡት ደስ ይለናል ።
ከዚህ ውጭ ለ28ኛ ግዜ በኦክቶብር 20/2024 ዓ/ም እሁድ ቀን ለምናደርገው አመታዊ ድግስ የአቢሲንያ ካፌ ባለቤቶች ፣ ሳራና ተስፋዬ ለ3ኛ ግዜ ለመደገስ ቃል ገብተውልናል ። ስለሆነም ፣ ለነዚህ ታሪክዊ የእንቡጥ ማኅበር ጠበቆቻችን በእንቡጥ ማኅበርና ተማሪዎቻችን ስም ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን ።
ይኽን ይጫኑ : በዚህ በኦክቶብር 20 እሁድ ለሚውለው አመታዊ ድግሳችን ላይ ልጆች ፣ ዘመድ አዝማድ ፣ ጓደኞችን ይዛችሁ በመምጣት እንደተለመደው ቀኑን አብረን እድናደምቀው ተጋብዛችኋል ።
እስከዚያው ጌታ በቸር ያገናኘን !!
እንደምታውቁት ፣ የአምናውን ኦክቶብር 1/ 2023 ዓ/ም የምኒልክ ምግብ ቤት ነበር ለ3ኛ ግዜ ለ 200 ተጋባዦች ያዘጋጀልን ፣ ለደግነቱ ወሰን ለሌለው ወንድም ሰለሞንና ኤርሚያስ ከመለው ሰራተኛ ጋር ምስጋናችን ይድረሳችሁ እንላለን ። 
በዚኽ ላይ ድግሱን በነጻ ለማድመቅ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞቻችን እነ መዝሙር ዮሃንስ ፣ ፍጹም ምንዋልኩለት ፣ ሙና አለሙ ና አድማሱ ገ/እግዚአብሄር በአንድነት ፣ ተጋባዡን በያመቱ ህጻን አዋቂውን ያስደስቱታል ። በተለይ ታዳጊ ህጻናት ከመርካቶ የተሽመቱን ቅርሳቅርሶች በቶምቦላና በጨረታ በማቅረብ የቀኑን ገቢ በያመቱ ከፍ እያደረጉት ነው ። ለምሳሌ ያኽል ፣ በዚህ ድግስ ቀን የ12 አመቷ ታዳጊ ሄሜላ ዘውዴ ለጨረታ የሚውል ስዕል አቅርባ የቀኑን ገቢ ከፍ በማድረጓ እጅግ ኮርተንባታል ። እንግዲህ ትብብራችን ምን ያኽል ጥግ ድረስ እንደሚሄድ ለማየት አያዳግትም ። ስለዚህ ሁሉንም ተባረኩ ብለናል ፣ አኩሪዎቻችን ናቸውና !!
እስካሁን ያለው አሃዝ እንደሚያመለክተው ፣ የእንቡጥ (Bourgeons) ማኅበር ከተመሠረተ ግዜ ጀምሮ የተከታተልናቸው ተማሪዎች ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እስከ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአስተማሪነት ፣ በሰዓሊነት ፣ በመኪና ሜካኒክ ፣ በፀጉር ስራ ፣ በጋራዥ ፣ በኮንፒተር ፣ በሂሳብ አያያዝ ፣ በባንክ ሥራ ፣ በፀሐፊነት በንግድ አለም ወዘተ በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ወደ 465 ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ሙሉ ተሳታፊ ለመሆን በቅተዋል ። ይኽ እንግዲህ ከ8ኛ እስከ 12ኛ ተምረው ራሴን በሚመስለኝ መንገድ ልምራ ብለው ትምህርታቸውን አቋርጠው በተለያየ የስራ አለም ውስጥ የተሰማሩትን በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ሳይጨምር ነው ።
ለቁም ነገር በደረሱ ሰአት ፣ የሚጽፉት የስንብት ደብዳቤ ባጭሩ ሲነበብ :- « ለዚህ ወግ ስላበቃችሁኝ እያመሰገንኩ ከቻላችሁ በኔ ቦታ ሌላ ወጣት ውሰዱ ። እኔ ደግሞ አቅሜ ከፈቀደ በወጣቶች ክለብ ውስጥ በመሳተፍ ሌሎቹን ለመርዳት ቃል እገባለሁ » ይላል ታድያ የዚህ ሁሉ አመት ግብግብ የማይሞተውን ትምህርት የተሰኝውን የዕውቀት ሀብት ለተማሪዎቻችን ለማውረስ ነውና ፣
ለነጻ አገልግሎት ሰጭዎቻችን የቢሮ ጓዶቻችን ፣ ለመላው አባላት ፣ (ፈረንሳይ ፣ ስዊዝ ፣ አሜሪካ) ፣ ለኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ፣ በርቱ ለሚሉን ወዘተ እንዲሁም የነዚህ ተማሪዎች የዕውቀት ምንጭ ለሆነው ዓድዋ በር ት/ቤት ታላቅ ምስጋና እናቀርባለን!
ጥያቄያቸው ምንድነው ?
የዓመት ፣ የት/ቤት መመዝገብያ ክፍያ ፣ መጽሐፍ ፣ ደብተር ፣ እርሳስ ፣ አጠቃላይ የዓመት ትምህርት ቁሳቁስ መግዣ ወዘተ የመሳሰሉት ናቸው ::
ይኽ ከተሟላላቸው የት/ቤት በርን በችግር ምክንያት ከማንኳኳት ዳኑ ማለት ነው ::
ከዚህ ውጭ የማኅበሩ አቅም በፈቀደ ቁጥር ባጀት ታይቶ ት/ቤቱ የጎደለውን ነገር በጠየቀን ግዜ ከሟሟላት ወደኋላ ብለን አናውቅም ።
ስለዚህ ፣ በእንቡጥ ማኅበር ጥላ ሥር ሆነው ለሚማሩ ተማሪዎች ፣ የተጀመረላቸው ዕርዳታ በችግር ምክንያት የመቋረጥ እድል እንዳይገጥመው የድርሻዎትን ያበርክቱላቸው ፣ ላልሰሙ አሰሙ !!
በተማሪዎቻችን ስም ሆነን ከጎናችን ለቆማችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋና እናቀርባለን ።
ከእንቡጥ ማኅበር ቢሮ


2023/ዓ/ም : የ27 ኛ ዓመት የእንቡጥ ማኅበር ድግስ ቀን ለማየት ይኽን ይጫ


ለእንቡጥ ድግስ ቀን የሳለችውን ስዕል ለቶምቦላ ና ለጨረታ ያቀረበችው የ12አመቷ ታዳጊ ሄሜላ ዘውዴ ይኽች ናት


ፈረንሳይ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታላቅ ርዳታ 400 ኪ/ግ የሚመዝን መድኃኒትና ተሽከርካሪ ወንበር ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች እንዲሁም ዐድዋ በር ት/ቤት ላሉት ተማሪዎች ትምህርት ሰጭ ዕቃዎችን ይዘው በተግባር ለማዋል የእንቡጥ (Bourgeons ) ማኅበርን ወክለው ወ/ሮ ካሚይ (መላኳ) ና አቶ ደጀን ይርጉ በጥቅምት ወር 2022 ዓ/ም ላይ ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉዞ የሚያመለክት በምስልና ቪድዎ የተደገፈ ይመልከቱ ።
https://photos.app.goo.gl/75tJ7YS4RuycRPFu8

በዚሁ ወቅት ወ/ሮ ካሚይ (መላኳ) ና አቶ ደጀን ይርጉ የእንቡጥ ማኅበርን በወከል በዐድዋ በር ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ከት/ቤቱ ኃላፊዎች ፣ ሰራተኞች ፣ የተማሪ ወላጆች ፣ ተማሪዎች ፣ እንዲሁም ከእንቡጥ (Bourgeons ) ወጣቶች መረዳጃ ማኅበር ጋር የነበረውን ግኑኝነት የሚያሳይ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ወገን ለወገን በሚል በሚደረገው የመረዳዳት ዘመቻ ዙርያ የኢትዮጵያ ARTS TV ያቀነባበረውን የ2ት ዙር የፊልም ቀረጻ ይመልከቱ ።

ARTS TV N°1
https://youtu.be/36P6r5Onffs

ARTS TV N°2
https://youtu.be/gQwUMKvEzso

በእንቡጥ ማኅበር ጥላ ስር ሆነው የሚማሩ የ2014 (2022) ዓ/ም ተማሪዎች አልበም ፎቶ

የተማረ ትውልድን ማፍራት አገርን ማዳን ነው !!

የሚጽፍ የሚያነብ የሚያሰላ ትውልድ ይመራመራል ፣
ለምን የሚለውንም ግንዛቤ ያገኛል ።
ከዚኽም አልፎ ቤተሰብና አገርን ይመራል ።

ስለዚህ ፣ ይኽን ዕድል እንስጣቸው !!

ከ465 ተማሪዎች ውስጥ የእንቡጥ ማኅበር በትምህርት አሳድጎ ለቁም ነገር ካበቃቸው ወጣቶች አንዱ ዘመኔው ይማኖ ሲሆን ፣ በአሁን ግዜ በመንግስት ት/ቤት የሂሳብ መምህር ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል ። የሁላችንም ምሳሌ ስለሆነ ተግባሩን በቪድዮ ይመልከ

በአድዋ በር ት/ቤት የእንቡጥ ማኅበር 20ኛ የልደት ክብር ቀን በሙዚቃ መምህሩና የወጣቶች ክለብ ኃላፊ በሆነው ዘላለም እንድርያስ የተዘመረ

የእንቡጥ ማኅበር ሕይወት በምስል ፣ በቪዲዮ ፣ በ ራዲዮ ቃለ ምልልስ ዙርያ

በእንቡጥ ማኅበር ጥላ ስር ኾነው የሚማሩ ተማሪዎች 2022_2023 ዓ/ም

የዓ ድዋ በር ት/ቤት የነበረው ገጽታ በፊትና በኋላ ከእንቡጥ ማኅበር ጋር የመጀመርያው ትውውቅ በቪድዮ 1994-1998 ዓ/ም


የሂሜላ የስራ ውጤት

_____________________________________________________________________________

አጋር የእንቡጥ ማኅበር የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች ድረገጽ

ፓሪስ
:
ጎጆምኒሊክአቢሲኒያ ካፌኢትዮጵያ ሐበሻእንጦጦለንጉስ ለላክ ጣና አጼ ቴዎድሮስአዲስ አበባሌሳቨር ደአቢሲኒእቴጌ ጣይቱ ኢትዮ-ሳሪስ ... ስዊዝ : አቢሲኒያ-ሎዛንአቢሲኒያ-ሲኦአቢሲኒያ ነሻቴልአቢሲኒያ-በርን አቢሲኒያ-ፍሪቡር ---- አሜሪካ - ዳላስ : ቡክሪ ካተሪንግ

_____________________________________________________________________________

የእንቡጥ ማኅበር አድራሻ - Association BOURGEONS 27 André Tessier 94120 France | | የማኅበሩን ዓላማ ለሌላው በማስተዋወቅ እንርዳ ። የእድሳት ቀን ሠኔ - ፩ - ፳፻፲፮ ዓ/ም

_____________________________________________________________________________