የተማረ ትውልድን ማፍራት አገርን ማዳን ነው !!

‘’ እንቡጥ’’ (Association Bourgeons) በበጎ ፈቃደኝነት ተነሳሺነት ፣ በፈረንሳይ እና በሲዊዘርላንድ ኗሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያኖችና በፈረንሳይ ተወላጅ ጓደኛሞች መካከል በኢትዮጵያ ውስጥ በችግር ላይ ወድቀው ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎችና ት/ቤቶች ፣ ያለባቸውን ችግር አብረዋቸው ለመካፈል ፣ የፈረንሳይ 1991 ዓ/ም ሕግ በሚፈቅደው መሠረት በአውሮፓውያን ቀን አቆጣጠር በ ሐምሌ 18 – 1996 ዓ/ም « Association Bourgeons » ፣ ሲነበብ ‘’ቡርዦ’’ ሲተረጎም ደግሞ ‘’ እንቡጥ’’ በሚለው ስም ማኅበሩ ተሰይሞ ተቋቋመ :: በዚህ ሕግ አንቀጽ 1901 ስር የሚተዳደሩ ማኅበሮች ምንም የመተዳደሪያ ገቢ የሌላቸው ወይም በንግድ ዓለም ተሰማርተው አትራፊ ያልሆኑ  ግብረሰናይ ማኅበሮች ናቸው ::
 

የአድዋ ብር ተማሪዎች ከማኅበሩ አባል ጋር
+
የዓመታት ልምድ

+
ልጆች በትምህርታቸው የተደገፉ
ብቃት እና ሥራ ያላቸው ወጣት ባለሙያዎች
በእንቡጥ የሚደገፉ ልጆች

የእኛ ተልዕኮ

የሚጽፍ የሚያነብ የሚያሰላ ትውልድ ይመራመራል ፣
ለምን የሚለውንም ግንዛቤ ያገኛል ።
ከዚኽም አልፎ ቤተሰብና አገርን ይመራል ።

እንዴት መርዳት እንደሚቻል

01.

ልጅን ስፖንሰር ማድረግ

ቀጥተኛ ለልጅ የትምህርት ድጋፍ ያቅርቡ

ልጅን ስፖንሰር ማድረግ

02.

ልገሳ አድርጉ

የተቻላችሁን በመለገስ ለአላማው አስተዋጽዎ ያርጉ

ልገሳ

03.

አባል ይሁኑ

የድጋፍ ማህበረሰባችንን ይቀላቀሉ

አባል ይሁኑ

እኛ ልዩ የሚያረገን

ቀጥተኛ ድጋፍ

እያንዳንዱ ልገሳ ለተቸገሩት ልጆች ግልጽ በሆነ አጋርነት በቀጥታ መድረሱን እናረጋግጣለን።

አጠቃላይ ግልጽነት

እያንዳንዱ ገንዘብ በሃላፊነት እና በብቃት ለህጻናት ትምህርት ጥቅም ላይ መዋሉን በማረጋገጥ ተግባራችን በኢትዮጵያ በስዊዘርላንድ እና በፈንሳይ በተመረጡ አባላት መሪዎች ቁጥጥር ስር ነው።

ሰዋዊ ግንኙነት

የማህበሩ አባላት ከትምህርት ቤቱ እና ከልጆች ጋር የመተማመን ግንኙነትን ለመጠበቅ እና ስለእድገታቸው ተጨባጭ ዜና ለማምጣት በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ።

አጋሮቻችን

Scroll to Top